የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማቀላጠፍ የከፍተኛ አመራሮች ሽግሽግና ምደባ ማድረጉን ተከትሎ በክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የአመራር የሥራ ርክክብ ተከናወነ።
መስከረም 23 ቀን 2019 በተካሄደው የሥራ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት፣ የቀድሞው የቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ መሐመድ ያህያ የኃላፊነት መንበራቸውን ለተኪያቸው ለክቡር አቶ ሃምዲ ሰላዲን አስረክበዋል።
በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት የቢሮው አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ በተገቢው መንገድ የተከናወኑና በሂደት ላይ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎችና ሰነዶች ልውውጥ ተደርጓል።
ይህ የተካሄደው የአመራር ምደባና ሽግሽግ የክልሉ መንግሥት የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥረቶችን በላቀ ሁኔታ ለማስቀጠል የሚያደርገው ጥረት አካል መሆኑ ተመልክቷል።
በሥነ-ሥርዓቱ ማጠቃለያም ለአዲሱ ተሺሚ ቢሮውን ወደተሻለ የዕድገት ደረጃ ለማሸጋገር ለሚያደርጉት ጥረት፣ እንዲሁም ለነባሩ አመራር ላበረከቱት አስተዋጽዖ የማንቀሳቀሻ መልካም የሥራ ዘመን ምኞት ተ አስተላልፏል።






