Harari BoFEC
No Result
View All Result
  • ዋና ገፅ
  • ቢሮው
    • ስለ እኛ
    • የቢሮ ሃላፊው መልዕክት
    • የስራ ክፍሎች
  • ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች
    • የቻናል አንድ ፕሮግራም
    • የተቀናጀ የበጀትና የወጪ መረጃ ሥርዓት (IBEX)
    • የፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂነት (FTA)
  • ሰነዶች
  • ሚዲያ
    • አምዶች
    • የፎቶ አምዶች
    • የቪዲዮ አምዶች
    • መፅሄቶች
  • ሃሳብ መስጫ
  • ዋና ገፅ
  • ቢሮው
    • ስለ እኛ
    • የቢሮ ሃላፊው መልዕክት
    • የስራ ክፍሎች
  • ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች
    • የቻናል አንድ ፕሮግራም
    • የተቀናጀ የበጀትና የወጪ መረጃ ሥርዓት (IBEX)
    • የፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂነት (FTA)
  • ሰነዶች
  • ሚዲያ
    • አምዶች
    • የፎቶ አምዶች
    • የቪዲዮ አምዶች
    • መፅሄቶች
  • ሃሳብ መስጫ
No Result
View All Result
Harari BoFEC
ሃሳቦን ይስጡ
No Result
View All Result

በሐረሪ ክልል የመሠረታዊ አገልግሎቶችን ጥራትና ተጠያቂነት ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

October 9, 2026
in መድረኮች, ወቅታዊ
0

ሐረር (መስከረም 28 ቀን 2019 ) ገኢትቢ— የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የመሠረታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን፣ ተደራሽነትንና ፍትሐዊነትን ለማሻሻል ያለመ የማህበራዊ ተጠያቂነት የግንዛቤ ማስጨበጫና የምክክር መድረክ አካሄደ።

መድረኩ በሕዝቡና በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል ቀጥተኛ የሐሳብ ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ የመንግሥት አገልግሎቶች የዜጎችን እውነተኛ ፍላጎት መሠረት ያደረጉና ተጠያቂነት የሰፈነባቸው እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ነው።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የጅንኤላ፣ አቦከር፣ አሚር-ኑር እና ሶፊ ወረዳዎች አመራሮች፣ አፈ-ጉባዔዎች፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሙያዎች፣ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሕያ አብዱረሒም እንደገለጹት የኢትዮጵያ ማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም በፌዴራል መንግሥትና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ትብብር የሚተገበር ወሳኝ አሠራር ነው። አሠራሩ በተለይም በውሃ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና እና በገጠር መንገድ ዘርፎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ደረጃ በየጊዜው ለመገምገምና ክፍተቶችን ለመሙላት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል።

ምክትል  ቢሮ ኃላፊው አክለውም ይህ ሥርዓት ኅብረተሰቡ በአካባቢው በሚከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ጥያቄዎችን በግልጽ እንዲያነሳ  የአገልግሎት ጉድለቶችን እንዲያመላክትና በመፍትሔ አፈላላጊነት በባለቤትነት እንዲሳተፍ ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

በመድረኩ የማህበራዊ ተጠያቂነት፣ የበጀትና የፋይናንስ ግልጽነት እንዲሁም የቅሬታ አፈታት ሥርዓትን የተመለከቱ ገለጻዎች ቀርበዋል። በተጨማሪም የጅንኤላ ወረዳ የተሞክሮ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የወረዳ አስተዳዳሪዎችም የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበው የማሻሻያ ግብረ-መልስ ተሰጥቷቸዋል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአራቱ ወረዳዎች የሚስተዋሉ የአገልግሎት አቅርቦት ማነቆዎችን በጋራ በመለየት አፋጣኝ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን አመላክተዋል። በመጨረሻም የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዜጎች ችግሮችን ያለምንም ማመንታት በግልጽ በማንሳትና የመፍትሔ ሐሳቦችን በማጋራት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ShareTweetShare

ተመሳሳይ አመዶች

ብዝሃነትን ማክበርና በምክክር አንድነትን ማጠናከር ለጠንካራ የፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።  ህዳር 4/2019 /ገኢትቢ/
ልዩ ልዩ

ብዝሃነትን ማክበርና በምክክር አንድነትን ማጠናከር ለጠንካራ የፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ። ህዳር 4/2019 /ገኢትቢ/

November 13, 2026
የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በፕሮግራም በጀት ዝግጅት ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ  ሐረር – ጥቅምት 19/2019
ስልጠናዎች

የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በፕሮግራም በጀት ዝግጅት ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ ሐረር – ጥቅምት 19/2019

October 31, 2026
የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ100 ቀናት ዕቅድ የ15 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ። – ጥቅምት 17/2019
ሌሎች

የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ100 ቀናት ዕቅድ የ15 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ። – ጥቅምት 17/2019

October 28, 2026
የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2019 የመጀመሪያ ሩብ ዓመትና የ100 ቀናት ዕቅድ ዝግጅትን ገመገመ።
ሌሎች

የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2019 የመጀመሪያ ሩብ ዓመትና የ100 ቀናት ዕቅድ ዝግጅትን ገመገመ።

October 9, 2026
የሀረሪ ክልል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በሰው ሐብት ትግበራ ፕሮግራም (Human Capital Operation)  የ2019 በጀት ዓመት የቅድመ ዝግጅት ውይይት አካሄደ።
መድረኮች

የሀረሪ ክልል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በሰው ሐብት ትግበራ ፕሮግራም (Human Capital Operation)  የ2019 በጀት ዓመት የቅድመ ዝግጅት ውይይት አካሄደ።

October 3, 2026
በሀረሪ ክልል በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የአመራር የሥራ ርክክብ ተከናወነ።
ልዩ ልዩ

በሀረሪ ክልል በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የአመራር የሥራ ርክክብ ተከናወነ።

October 3, 2026
Load More
Next Post
የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2019 የመጀመሪያ ሩብ ዓመትና የ100 ቀናት ዕቅድ ዝግጅትን ገመገመ።

የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2019 የመጀመሪያ ሩብ ዓመትና የ100 ቀናት ዕቅድ ዝግጅትን ገመገመ።

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

  • About
  • Help
  • Feedback
  • Contact
Call us: + 251 666 0955

Copyright @ 2022 HPRS Bureau of Finance and Economic Corporation , All Rights Reserved